ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 'የዕርቅ ሀሳብ አለኝ' ፕሮግራም የዕወቅናና የማበረታቻ ፕሮግራም በካፒታል ሆቴል ተካሂዷል9/21/2020 ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 'የዕርቅ ሀሳብ አለኝ' መርኃግብር ፕሮግራም የዕወቅናና የማበረታቻ ፕሮግራም ዛሬ በካፒታል ሆቴል ተካሂዷል።
በመርኃግብሩ በተሳታፊዎች ከተሰሩ ሥራዎች መካከል 7 የሚሆን የተለያዩ የሥራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። ገዲዝም የተሰኘ ከተሳታፊዎች የተገኘ አንድ ጹሑፍ ላይ መሰረት ያደረገ በአኒሜሽን የተሰራ ትዕይንትም ለዕይታ ቀርቧል። የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስን ጨምሮ በመድረኩ የተገኙ እንግዶች ለተሳታፊ ወጣቶች መልዕክትና ምሥጋናቸውን አቅርበዋል። በዕለቱ ጭውውቶች አነቃቂ ንግግሮችና የመዝናኛ ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን በፕሮግራሙ መጨረሻ ላይ በአቀራረባቸው አሸናፊ ለሆኑ ለግልና የቡድን ተሳታፊዎች ሽልማቶች ተሰጥተዋል። የተሸለሙ አሸናፊዎች ጥቂቶች ቢሆኑም እንደ ሥራቸውና እንደ ጥረታቸው ሁሉም ሥራዎች (ከ360 በላይ ጹሑፎች) አሸናፊዎች ናቸው። በቀጣይም በዛሬው ዝግጅት ብቻ ይህ ተሳትፎ እንዳይቆምና እንዲቀጥል በመግባባት ላይ ተደርሶ የዝግጅቱ ፍጻሜ ሆኗል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ጋር በትብብር ይህንን ዝግጅት ሲያዘጋጅ ወጣቶች እድል ቢያገኙ ትልቅ አበርክቶ እንዳላቸው እንዲሁም እውቀትና ጉልበታቸውን ተጠቅመው በዕርቅ ውስጥ መሳተፍ እንደሚችሉ ማሳያ ይሆን ዘንድ ነው። ይሄንንም ፕሮጀክት ጨምሮ በወጣቶች ዙሪያ የምንሰራቸውን ስራዎች ወደፊትም አጠንክረን የምንቀጥል ይሆናል። ረጅም ርቀት አቋርጣችሁ ከተለያዩ አከባቢዎች የተገኛችሁ እንዲሁም ይህ ሥራ ዕውን እንዲሆን ለደከማችሁ የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትና ሰራተኞች በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። |
Archives
November 2020
Categories |