የኢትዮጵያ እርቀ ሰላም ኮሚሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በአገሪቱ እየተከሰቱ ያሉ ዘርን ማእከል ያደረጉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች መኖራቸውን ተወያይቷል። በምእራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ጋንቃ ቀበሌ፣ በጉራፈርዳ እና በመተከል ዞን ምንም በማያቁና ምንም አይነት የፖለቲካ ግንኙነትና እንቅስቃሴ በሌላቸው ንፁሃን ዜጎች ላይ የደረሰው ዘግናኝ ግድያ በእጅጉ አሳዛኝና የሚያስቆጣ ሆኖ አግኝቶታል።
ይህ አንድን ዘር ማእከል አድርጎ የተፈፀመ የጅምላ ግድያ ከመሆኑም በላይ ኢሰብአዊ ድርጊት በመሆኑ ኮሚሽኑ ድርጊቱን ያወግዛል። መንግስት ይህን ድርጊት በፈፀሙ ቡድኖች ላይ አስቸኳይ እርምጃ በመውሰድ አጥፊዎቹን ለፍርድ እንዲቀርብ ኮሚሽኑ አጥብቆ ይጠይቃል። ከግድያው ጋር በተያያዘ ባደረባቸው ስጋትና ፍርሃት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ዋስትና በመስጠት መልሰው እንዲቋቋሙ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን። እንዲህ አይነት ዘግናኝ ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ቡድኖችም ንፁሃን ዜጎችን ለፖለቲካ ቁማር ለማዋል ሲባል ኢ ሰብአዊ ድርጊት ከመፈፀም ተቆጥበው በሰላም በመግባባትና በድርድር የሚንቀሳቀሱበትን ሁኔታ ማሰብ እንዳለባቸው እናስገነዝባለን። ምንም በማያውቁት ሁኔታ በጅምላ የተገደሉ ንፁሃን ዜጎችን ፈጣሪ ነፍሳቸውን እንዲምር በመማፀን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን። |
Archives
November 2020
Categories |