• Home
  • News
    • Press Release
    • Press Conference
  • Event
  • Complaint Information
  • Videos
  • About
    • Members
    • Gallery
  • Contact
ETHIOPIAN RC
  • Home
  • News
    • Press Release
    • Press Conference
  • Event
  • Complaint Information
  • Videos
  • About
    • Members
    • Gallery
  • Contact

“እኔም የዕርቅ ሀሳብ አለኝ “ የሚል ወጣቱን አሳታፊ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ፡፡

5/21/2020

Comments

 
Picture

የዕርቀ ሠላም ኮሚሽን ሕብረተሰቡ በዕርቅና በሠላም ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ የተለያዩ ዕቅዶችን ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ይህንን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ‘ቲክቫህ ኢትዮጲያ’  ከሚባል የቴሌ ግራም ቻናል ጋር በመተባበር ወጣቱን አሳታፊ የሆነ ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል፡፡ በርካታ ተከታዮች ያሉት ቻናሉ ወጣቱ በተለያዩ መስክ ያለውን እምቅ ችሎታ ተጠቀሞ  በየአካባቢያቸዉ ያለዉን ሰላምንና ዕርቅን ማስፈን ሚችሉ ሀገር በቀል እዉቀቶችንና የዕርቅ አፈታት ስርዓቶችን  እንዲለዩና ለሌላዉ ማህበረሰብ ክፍል እንዲያሳዉቁ የሚያስችል ነዉ፡፡ 
የገፁ አስተባባሪ ወጣት በረከት ጉዲሳ እንደተናገረዉ ወጣቱ የተለያዩ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎችን ተጠቅሞ በየአካባቢያቸዉ ያለዉን የዕርቀ ሠላም ሀሳቦችን በተቀመጠባቸዉ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
 
ፕሮጀክቱን በይፋ ያስጀመሩት የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል ይህ ‘ቲክቫህ ኢትዮጲያ’ አስተባባሪ ወጣቶች የያዙት ሀሳብ ከዕርቀ ሠላም ኮሚሽን ተልዕኮ ጋር በእጅጉ የሚገናኝ ስለሆነ ኮሚሽኑ ወጣቱን የሕብረተሰብ ክፍል ለሰብዓዊ አገልግሎትና ለእርቀ ሰላም ለማነሳሳት ከዚህ  ማህበራዊ ሚዲያ ጋር መስራት ጥሩ አማራጭ ነዉ ብለዋል፡፡
​
ወጣቱ ምንም እንኳ በሚከሰቱ ግጭቶች ቀዳሚ  ተሳታፊና ቀዳሚ ተጎጂ ቢሆንም የሰላም ግንባታ ዉስጥ ተሳታፊ እንዲሆን የሚደረገዉ እንቅስቃሴ ክፍተኛ የሚባል አይደለም፡፡  እንዲሁም በአካባቢዉ ያሉትን አገር በቀል የሠላም  እሴቶች እና የዕርቅ ስርአቱን የሰላም እንዲያዉቁ ሲደረግ አይስተዋልም፡፡ ክዚህ ባሻገር ወጣቱ የዕርቅና የሰላም እሴቶች እንዲተገብራቸዉና እንዲያዉቃቸዉ የሚስችል መደላደል አልተነደፈለትም፡፡  ይህ ከቲከቫህ የሚደረግ ፕሮጀክት እነዚህን በማህበረሰቡ ወስጥ የሚገኙ የዕርቅ ስርአቶች ወጣቱ እንዲመረምር እንዲያዉቅና በመረጃ የተደገፈ ጥናት እንዲያደርግ ያስችላል፡፡

Comments

    Archives

    November 2020
    October 2020
    September 2020
    August 2020
    July 2020
    June 2020
    May 2020
    March 2020
    February 2020
    September 2019

    Categories

    All
    News

    RSS Feed

Picture
                          Social Media
                              Facebook : ERC
​
                              
Twitter : ERC

        © 2020 Ethiopian Reconciliation Commission​​
  • Home
  • News
    • Press Release
    • Press Conference
  • Event
  • Complaint Information
  • Videos
  • About
    • Members
    • Gallery
  • Contact