የተከበሩ ካዎ ደምሴ የዚጊቲ የጋሞባኮሌ አካባቢ ባህላዊ ንጉሥ: ቀደም ሲል በገሙ ተከስቶ የነበረውን ግጭትና የበቀል ተነሳሽነትን ለማብረድና ሰላም ለመፍጠር ሣር ይዘው በመንበርከክ ወጣቱን ከጥፋት እንዲመለስ በባሕላዊው ችግር አፈታት እርቅ እንዲወርድ ይስስተባበሩት ካዎ ፋራ ነበሩ::
ካዎ ደምሴ ባደረባቸው ሕመም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ቅዳሜ ሐምሌ11 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል:: ቀብራቸው እሁድ ሐምሌ 12 2012 ዓም በባሕላዊው የቀብር ሥርአት መሰረት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት በአካባቢው ባለው የአቦ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል:: የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡ |
Archives
November 2020
Categories |