የኢትዮጵያ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ከአንድ ዓመት በፊት የተቋቋመ ሲሆን፣ የስትራተጂክ ዕቅድ ዝግጅትን፣ ከአያሌ ተቋማት እና ቡድኖች ጋር በአጋርነት መሥራትን፣ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ የባለድርሻ አካላት ምክክሮችን ማካሄድ እንዲሁም በአንዳንድ የሀገራችን ክፍሎች ግጭት ሲከሰት የመፍትሔ እንቅስቃሴዎችን ማድረግን ጨምሮ፣ ከተቋቋመ ወዲህ የተሠሩትን ሥራዎች አስመልክቶ ለመወያየት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተዋል። በኮሚሽኑ ተወካዮች አማካኝነት የቀረቡትን ዐበይት የክንውን ምዕራፎች ተከትሎ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልካም ፈቃደኝነትን መነሳሳት በመፍጠር አቅማቸውን እና ብቃታቸውን በማጎልበት ተግባራቶቻቸውን በተሻለ ለማጠናከር እና ቁልፍ ተግባራትን ለመከወን በሚችሉባቸው መንገዶች ላይ አቅጣጫን አመላክተዋል። Members of the Ethiopian Reconciliation Commission established one year ago met with Prime Minister Abiy Ahmed to discuss and review progress of activities undertaken, including the development of a strategic plan; forging partnerships with various entities and groups; stakeholder consultations in different areas and taking targeted interventions following conflict in some pockets of the country.
After reviewing the key milestones presented by representatives of the commission, Prime Minister Abiy provided direction in how to further strengthen their activities by focusing on the capacity and potential of the commission to execute key activities through creating goodwill. |
Archives
November 2020
Categories |