የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰኔ 18/2012 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በእርቀ ሰላም ኮሚሽን በተጓደሉ አባላት ምትክ አምስት የኮሚሽን አባላትን ሾሟል፡፡ እነዚህም፡-
የእርቀ ሰላም ኮሚሽን በ41 የኮሚሽን አባላት የሚመራ እና በህዝቦች መካከል በእውነትና ፍትህ ላይ የተመሰረተ ዕርቅ እንዲሰፍን የሚሰራ በአዋጅ ቁጥር 1102/2011 የተመሰረተ ተቋም ነው፡፡ የእርቀ ሠላም ኮሚሽን አባላት በአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር ላይ ያደረጉትን ተሳትፎ የሚያሳይ በኢትዮጰያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቀረበ ሪፖርት6/23/2020 የእርቀ ሠላም ኮሚሽን አባላት እና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራን መረሃ ግብር ከግብ ለማድረስ ዛሬ ጽ/ቤቱ እና በእንጦጦ አረንጓዴ ፓርክ ችግኝ ተከላ አካሂዷል፡፡
የኮሚሽኑ አባላት ከ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ጽ/ቤት ሠራተኞች እንዲሁም ከአዲስ አበባ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በመሆን በኮሚሽኑ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ እና በእንጦጦ አርንጓዴ ባርክ ችግኝ ተክለዋል፡፡ የኮሚሽኑ ዋና ሰብሳቢ ብፅዕ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፊል የአረንጓዴ አሻራ ስኬት በአገሪቱ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ስለሚኖረው ሁሉም ሊተባበር ይገባል ብለዋል፡፡ የእርቀ ሠላም ኮሚሽን ከአዲስ አበባ፣ አምቦ፣ ወሎንኮሚና ሀዋሳ ከተማ የተውጣጡ በጐ ፈቃደኛ ወጣቶች እርስ በእርሳቸው እንዲተዋወቁ እና በዕርቀ ሠላም ሃሳብ ዙሪያ በጋራ በሚሠ\በት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ትብብር መሥራች ኦባንግ ሚቶ ወጣቶች ሰው በመሆናቸው ብቻ ከሌሎች ወጣቶች ጋር በጋራ የመቆም መንፈስ በሚያጎለብቱበት ሁኔታ ላይ የማነቃቂያ ንግግር አድርገዋል፡፡ የእርቀ ሠላም ኮሚሽን አባል አቶ ታም\ ለጋ ስለ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ሚና፣ እስካሁን ስላካሄዱት ተግባር ወደፊት ስለሚሠ\ባቸው ተግባራት ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡ “ወጣት ለወጣት ለዕርቀ ሠላም” በሚል በበጐ ፈቃደኛ ወጣት ሄኖክ ባዮ ባዘጋጀው ወጣቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው በሚያስችል ፅሑፍ ላይ ተወያይተዋል፡፡ ከአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ የተወጣጡ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ለሐዋሳ ወጣቶች የኮቪድ - 19 መከላከያ የሚሆን የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አበረከቱ፡፡6/11/2020 ከአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ /ኦሎንኮሚ እና አምቦ/ የተወጣጡ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ለሐዋሳ ወጣቶች የኮቪድ - 19 መከላከያ የሚሆን የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አበረከቱ፡፡
“ወጣት ለወጣት” በሚል ሃሳብ ወደ ሐዋሳ የተንቀሳቀሱት ወጣቶች በከተማዋ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ደማቅ አቀባበል ተደርጐላቸዋል፡፡ በተጨማሪም በሚሊንየም አዳራሽ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች እስካሁን በየከተሞቻቸው ያከናወኑትንና ወደፊት ምን ሊያደርጉ እንዳሰቡ ውይይት አድርገዋል፡፡ “ችግር እንንቀል፤ ችግኝ እንትከል” በሚል እሳቤ በከተማው በሚገኘው ታቦር ተራራ ላይ በጋራ ችግኝ ተክለዋል፡፡ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ያደረጓቸው የመተሳሰብ እና የመደጋገፍ የቆየ ባህላችን መጠበቅና ወደፊትም ለሠላም ግንባታው ወጣቱ መሪ በመሆን የጎላ ድረሻ እንዲወጣ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ አሳስበዋል፡፡ የዕርቀ ሠላም ኮሚሽን ወጣቶቹ ያካሄዱት የተቀደሠ ተግባር እንዲጠናከር ድጋፉን እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ ከአዲስ አበባ እና ከኦሮሚያ ኦሎንኮሚና አምቦ ከተሞች የተወጣጡ ወጣቶች ‹‹ ወጣት ለወጣት ›› በሚል መርህ ለሐዋሳ ወጣቶች ኮቪድ 19 ለመከላከል የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን ለማበርከትና ያለውን መልካም ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል ጉዞ ጀምረዋል፡፡
ከአዲስ አበባ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ጽ/ቤት ሲነሱም በእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል እና ከኦሮሚያ በመጡ አባገዳ ገመዳ ሁንዴ አሸኘኘት ተደርጓል፡፡ |
Archives
November 2020
Categories |