• Home
  • News
    • Press Release
    • Press Conference
  • Event
  • Complaint Information
  • Videos
  • About
    • Members
    • Gallery
  • Contact
ETHIOPIAN RC
  • Home
  • News
    • Press Release
    • Press Conference
  • Event
  • Complaint Information
  • Videos
  • About
    • Members
    • Gallery
  • Contact

October 18th, 2020

10/18/2020

Comments

 


የኢትዮጰያ እርቀሰላም ኮሚሽን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህት ሚኒሰቴር ጋር በጥናትና ምርምር፤ በማኅበረሰብ አገልግሎትና የኮሚሽኑን ተደራሽነት በማሳደግ ረገድ በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ሁለቱ ተቋማት ስምምነቱን የተፈራረሙት ኮቪድ-19ን እየተከላከሉ ከፍተኛ ትምህርትና ስልጠናን የማስቀጠል የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ ግምገማ መድረክ ላይ ሁሉም የዩኒቨረሲቲ ፕሬዚዳንቶች፤ የቦርድ አምራሮች፤ ሚኒስትሮች እና ሌሎች ክፍተኛ ሃላፊዎች በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ ነው፡፡
ስምምነቱን የእርቀሰላም ኮሚሽን ዋና ሰብሳቢ ብፅዕ ካርዲናል ብረሃነእየሱስ ሱራፌል እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ፈርመዋል፡፡

ዛሬ ሁለቱ ተቋማት የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት በተልይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ባላሙያዎችን በመጠቀም በተመረጡ ግጭቶች ዙሪያ መሠረታዊ መነሻ ምክንያታቸውን የመለየትና ከአገር ውስጥና ከዓለም አቀፍ ልምድ በመነሳት ተመራጭ የግጭት አፈታት ስልቶችን የሚያመለክቱ ጥናቶችና ምርምሮችን ለማድረግ ያስችላል፡፡

ስምምነቱ በአገራችን ለበርካታ ዓመታትና በተለያዩ የመንግስት ሥርዓቶች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲከሰቱ ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን የመለየትና ለወደፊቱ ምን ተግባራትን በመፈጸም ዳግም እንዳይከሰቱ ማድረግ እንደሚቻል አመላካች ጥናትና ምርምር ለማድረግና በተለዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ የሚደረጉ የማጣራት ተግባራት ላይ ሙያዊ እገዛ ለመስጠትንም ያስችላል፡፡

በተለይ ሁለቱ ተቋማት በተናጠል የሚያድረጓቸው ተመሳሳይ ስራዎችን በመሰብሰብና የጋራ ማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እቅድ በማዘጋጀት የሥራ ድግግሞሽን፣ ድካም አና አላስፈላጊ የሃብት ብክንትን ለማስቀረት ያስችላል ተብሏል፡፡

ኮሚሽኑ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተደራሽነቱን ለማሳደግ እንዲያግዘው በመጀመሪያ ዙር ሊከፍት ላሰበው በአዲስ አበባ፣ መቀሌ፣ ባህር ዳር፤ ደሴ፣ ጂግጂጋ፤ ድሬዳዋ፣ አሰላ፣ ሃዋሳ፣ አርባ ምንጭ፣ ጅማ፣ ነቀምቴ፣ አሶሳ እና ጋምቤላ ጽ/ቤቶች በእነዚህ ከተሞች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለጽ/ቤት የሚሆኑ ክፍሎችን በማዘጋጀት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡

በስምምነቱ ወቅት ስለእርቀ ሰላም ኮሚሽን አላማ፤ ግብና እስካሁን የመጣበትን ሂደት የኮሚሽኑ አባል አቶ ታምሩ ለጋ ገለፃ አቅርበዋል፡፡

Comments

የኢትዮጰያ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በሚሰራበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ ፡፡

10/9/2020

Comments

 
የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ዋና ሰብሳቢ ብፁእ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል እና ምክትል ሰብሳቢ ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ እንዲሁም የኮሚሽኑ ቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎች ስለሰራቸው ስራዎች ወደፊት ሊሰሯቸው ባሰቧቸው ተግባራት ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል፡፡ ኮሚሽኑ በተለይ በዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ወጣቶችን ተደራሽ ለማድረግና ስለ እርቀ ሰላም እሴቶች እንዲረዳ እና ለጋራ መግባባት እንዲጠቀሙባቸው የሚያስችሉ ስራዎችን ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር መስራት እንደሚቻል ጠቁሟል፡፡

በተለይ በቅርቡ ሊከፍታቸው ያሰባቸው 13 ፅ/ቤቶች መቀመጫቸው ገለልተኛ በሆኑ ተቋማት እንዲሆኑ በማሰብ ቢሮች በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሆኑ አቅዷል፡፡
ኮሚሽኑ የያዛቸው እቅዶች ለመፈፀምና የተጣለበትን ትልቅ ኃላፊነት ለመወጣት ከከፍተኛ የሳይንስና የትምህርት ሚኒስቴር ጋር መስራቱ ውጤታማ እንደሚያደርገው በማመኑ እንዲህ አይነት ውይይት እንዲካሄድ መፈለጉን ጠቁመዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶ/ር ሳሙኤል ዑርቃቶ እና የሚኒስቴሩ ዴታዎች እንደገለፁት በአገሪቱ የሚከሰቱ ግጭቶች አለመግባባቶች መሰረታቸው ምንድን ነው የሚለው በጥናት ምርምር በማድረግ ትክክለኛና ወቅታዊ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡

የሁለቱ ተቋማት በጋራ መስራት በዕውቀት ላይ የተመሰረተ የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የሰላም ግንባታ እና የእርቅ ሂደቶች የተሳካ ያደርገዋልም ብለዋል፡፡ በተለይ ወጣቱን ትውልድ በአገር ግንባታ ላይ ለመጠቀም የሚያስችሉ ስራዎች ቅድሚያ ተሰቷቸው ሊሰሩ ይገባል ተብሏል፡፡
የእርቀ ሰላም ኮሚሽንና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ሁኔታም ለመፍጠር የመግባቢያ ሰነድ ለማዘጋጀት እና የጋራ ስራዎችን ለመለየት እንዲቻል ከሁለቱም ተቋም የተወከሉ አንድ ኮሚቴ ሰይመዋል፡፡  
Comments

    Archives

    November 2020
    October 2020
    September 2020
    August 2020
    July 2020
    June 2020
    May 2020
    March 2020
    February 2020
    September 2019

    Categories

    All
    News

    RSS Feed

Picture
                          Social Media
                              Facebook : ERC
​
                              
Twitter : ERC

        © 2020 Ethiopian Reconciliation Commission​​
  • Home
  • News
    • Press Release
    • Press Conference
  • Event
  • Complaint Information
  • Videos
  • About
    • Members
    • Gallery
  • Contact