• Home
  • News
    • Press Release
    • Press Conference
  • Event
  • Complaint Information
  • Videos
  • About
    • Members
    • Gallery
  • Contact
ETHIOPIAN RC
  • Home
  • News
    • Press Release
    • Press Conference
  • Event
  • Complaint Information
  • Videos
  • About
    • Members
    • Gallery
  • Contact

October 18th, 2020

10/18/2020

Comments

 


የኢትዮጰያ እርቀሰላም ኮሚሽን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህት ሚኒሰቴር ጋር በጥናትና ምርምር፤ በማኅበረሰብ አገልግሎትና የኮሚሽኑን ተደራሽነት በማሳደግ ረገድ በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ሁለቱ ተቋማት ስምምነቱን የተፈራረሙት ኮቪድ-19ን እየተከላከሉ ከፍተኛ ትምህርትና ስልጠናን የማስቀጠል የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ ግምገማ መድረክ ላይ ሁሉም የዩኒቨረሲቲ ፕሬዚዳንቶች፤ የቦርድ አምራሮች፤ ሚኒስትሮች እና ሌሎች ክፍተኛ ሃላፊዎች በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ ነው፡፡
ስምምነቱን የእርቀሰላም ኮሚሽን ዋና ሰብሳቢ ብፅዕ ካርዲናል ብረሃነእየሱስ ሱራፌል እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ፈርመዋል፡፡

ዛሬ ሁለቱ ተቋማት የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት በተልይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ባላሙያዎችን በመጠቀም በተመረጡ ግጭቶች ዙሪያ መሠረታዊ መነሻ ምክንያታቸውን የመለየትና ከአገር ውስጥና ከዓለም አቀፍ ልምድ በመነሳት ተመራጭ የግጭት አፈታት ስልቶችን የሚያመለክቱ ጥናቶችና ምርምሮችን ለማድረግ ያስችላል፡፡

ስምምነቱ በአገራችን ለበርካታ ዓመታትና በተለያዩ የመንግስት ሥርዓቶች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲከሰቱ ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን የመለየትና ለወደፊቱ ምን ተግባራትን በመፈጸም ዳግም እንዳይከሰቱ ማድረግ እንደሚቻል አመላካች ጥናትና ምርምር ለማድረግና በተለዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ የሚደረጉ የማጣራት ተግባራት ላይ ሙያዊ እገዛ ለመስጠትንም ያስችላል፡፡

በተለይ ሁለቱ ተቋማት በተናጠል የሚያድረጓቸው ተመሳሳይ ስራዎችን በመሰብሰብና የጋራ ማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እቅድ በማዘጋጀት የሥራ ድግግሞሽን፣ ድካም አና አላስፈላጊ የሃብት ብክንትን ለማስቀረት ያስችላል ተብሏል፡፡

ኮሚሽኑ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተደራሽነቱን ለማሳደግ እንዲያግዘው በመጀመሪያ ዙር ሊከፍት ላሰበው በአዲስ አበባ፣ መቀሌ፣ ባህር ዳር፤ ደሴ፣ ጂግጂጋ፤ ድሬዳዋ፣ አሰላ፣ ሃዋሳ፣ አርባ ምንጭ፣ ጅማ፣ ነቀምቴ፣ አሶሳ እና ጋምቤላ ጽ/ቤቶች በእነዚህ ከተሞች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለጽ/ቤት የሚሆኑ ክፍሎችን በማዘጋጀት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡

በስምምነቱ ወቅት ስለእርቀ ሰላም ኮሚሽን አላማ፤ ግብና እስካሁን የመጣበትን ሂደት የኮሚሽኑ አባል አቶ ታምሩ ለጋ ገለፃ አቅርበዋል፡፡

Comments

    Archives

    November 2020
    October 2020
    September 2020
    August 2020
    July 2020
    June 2020
    May 2020
    March 2020
    February 2020
    September 2019

    Categories

    All
    News

    RSS Feed

Picture
                          Social Media
                              Facebook : ERC
​
                              
Twitter : ERC

        © 2020 Ethiopian Reconciliation Commission​​
  • Home
  • News
    • Press Release
    • Press Conference
  • Event
  • Complaint Information
  • Videos
  • About
    • Members
    • Gallery
  • Contact